በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ የብር ጌጣጌጥ፣ ፕላትኒየም፣ ጊርቦክስ፣ የመኪና ሞተር እና ሌሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 23/2018፣ 24/2018፣ 25/2018፣ 26/2018፣ 27/2018፣ 28/2018፣ 29/2018፣ 30/2018 የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ የብር ጌጣጌጥ፣ ፕላትኒየም፣ ጊርቦክስ፣ የመኪና ሞተር እና ሌሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ እና በግልጽ ጨረታ 23/2018 በቀን 03/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 06/2018 በቀን 24/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 25/2018 በቀን 10/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 26/2018 በቀን 13/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 27/2018 በቀን 17/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 28/2018 በቀን 20/02/2018 ዓ.ም፤ ጨረታ ቁጥር 29/2018 በቀን 24/02/2018 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 30/2018 በቀን 27/02/2018 ዓ.ም በመሆኑ የቀጣይ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ይህ ማስታወቂያ ዝርዝር መረጃው ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን፡፡
በመሆኑም፤
- በቅ/ጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00፤ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ ጥቅምት 03/2017 ዓ/ም፣ ጥቅምት 06/2018፣ ጥቅምት 10/2018፣ ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም ጥቅምት 17/2018፣ ጥቅምት 20/2018፣ ጥቅምት 24/2018 ዓ/ም እና ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፤ የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ፣ ፈርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒ.ኦ (CPO) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- በተራ ቁጥር 01 - 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 23/2018 በቀን 03/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 06/2018 በቀን 24/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 25/2018 በቀን 10/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 26/2018 በቀን 13/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 27/2018 በቀን 17/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 28/2018 በቀን 20/02/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 29/2018 በቀን 24/02/2018 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 30/2018 በቀን 27/02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
- በሐራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /መቶ ሺህ/ ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳውቃልን፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃልን፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር፡- 0116684537 እና 0116684193 ደውሎ ይጠይቁ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
