Tender Detail

Tender Details

  • Company የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
  • Address መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ወይም መገናኛ ሕዳሴ ህንጻ ወረድ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 157 0333
  • Websitehttps://www.poessa.gov.et/
  • Deadline25 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • opening date2025-10-25 00:00:00
  • Categories Office And Home Furniture , Vehicle tire , Office Equipment

የግል ድርጀት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ማለትም የተለያዩ ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸር፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ማስዋቢያ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የግል ድርጀት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ማለትም የተለያዩ ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸር፣ የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ማስዋቢያ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳዳሩ ተጋብዘዋል።

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ አለባቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጸውን ማናቸውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታው መውጣት አይችልም።
  6. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ስፔስፊኬሽን(ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣የተሽከርካሪ ጎማዎች እና ማስዋቢያ ዕቃዎች) ተወዳዳሪ ድርጀቶች ናሙና /ሳምፕል /ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በአስተዳደሩ ንብረት ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል። ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ኦሪጅናል መሆን አለባቸው።
  7. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸር) አስተዳደሩ በሚያቀርበው ናሙና/ሳምፕል መሰረት አሟልቶ ላልቀረበ ማንኛውም ሁኔታዎች ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የተጫራቾች /የአቅራቢው/ ድርጅት ይሆናል።
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO /ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና በአስተዳደሩ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  10. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 200 እስከ ቀኑ 1100 ድረስ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው 16ኛው የስራ ቀን 400 ታሽጎ በዚያው ዕለት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጂ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የቴከኒክና ፋይናንስ ሰነዶችን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልጽ መጻፍ ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ከቀረበ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።እንዲሁም በአስተዳደሩ ተዘጋጅቶ በጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሞላት አለበት።
  13. አሸናፊ ድርጅት ባሸነፈባቸው ዕቃዎች ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለድርጅቱ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  14. ጨረታው አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማሰር ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች በጨረታ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /cpo/ሲፒኦ/ ለአስተዳደሩ ገቢ ይደረጋል። አስፈላጊው አሰተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል።
  15. አስተዳደሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

.

 

የግዥው ዓይነት

 

የጨረታ ቁጥር

 

የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን

 

ሎት 1

 

ልዩ ልዩ መሣሪያዎች

 

የግድሠማዋአ /ብግጨ/001/007/2018

 

50,000.00 / ሃምሳ ሺህ ብር /

 

ሎት 2

 

የተሽከርካሪ ጎማዎች

 

የግድሠማዋአ /ብግጨ/001/08/2018

 

150,000 / አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር /

 

ሎት 3

 

ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች/ፈርኒቸር /

 

የግድሠማዋአ /ብግጨ/001/09/2018

 

100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር /

 

 

አድራሻችን፡- አዲስ አበባ መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ወይም የአስተዳደሩ ዋና /ቤት የግዥ ዳይሬክቶሬት 11 ፎቅ

ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር +251-111-56 88 90

 

የግል ድርጀት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

Save Tender