በየካ ከ/ከተማ ወረዳ 12 የካራ ጋቢሳ ቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018
በየካ ከ/ከተማ ወረዳ 12 የካራ ጋቢሳ ቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ሕጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት መስፈርቱን የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የሎት ዝርዝርና የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/በኢትዮ.ብር
ሎት1 የደንብ ልብስ—— -5000 ብር
ሎት2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች -3000 ብር
ሎት13. የኅትመት ዕቃዎች -2000 ብር
ሎት4. አላቂ የሕክምና ዕቃዎች -2000 ብር
ሎት5. አላቂ የት/ት ዕቃዎች 4000 ብር
ሎት6. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች -2000 ብር
ሎት7. ሌሎች አላቂ መሣሪያዎችና መጽሐፍት-2000 ብር
ሎት8. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች-10000 ብር
በጨረታ መሳተፍ በምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያስባችሁ
1. በዘርፋ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃና የምስከር ወረቀት እንዲሁም ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪም ከሬጅስተር ማሽን ደረሰኝ ያላቸው።
3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የካራ ጋቢሳ ቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ይችላሉ። ስለዚህ በተሰጠው ቀንና ሰዓት ሁሉም ተጫራቾችሰነዳቸውን አስገብተው ማጠናቀቅ አለባቸው::
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/CPO/ማስያዝ አለባቸው:: የመወዳደሪያ እቃ ዋጋ ከቫት ጋር ደምረው ሕጋዊ ማኅተምና ፊርማ አድርገውበት ይላኩልን፡፡
5. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
6.ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ኦርጂናልና ኮፒ አድርገው ማስገባት አለባቸው::
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ደረጃውን የጠበቀና ናሙና ለት/ቤቱ ማቅረብ አለባቸው::
8. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ መልሰው ትክከለኛውን ዕቃ የማምጣት ግዴታ አለባቸው::
9. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሽነፈበት ጨቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ /C.P. O/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታ ካራ ጋቢሳ የመጀ/ደ/ት/ቤት ከካራ ወደ ጣፎ ሲሄዱ በገደራ ሳራ አምፑል በግራ በኩል ገባ ብሎ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም ሳይት G7 መጨረሻ በስተግራ ታጥፎ 4.5 ኪሜ ገባ ብሎ ስዲስ አበባ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-8-68-04-87/09-33-73-85-04 ደውለው ይጠይቁ ።
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የካራ ጋቢሶ ቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
