የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ውስጥ ለሚሰሩ የመንግሥት ሠራተኞች መዝናኛ እና ለጤና አጠባበቅ አገልግሎት የሚውል ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የጂም (GYM) አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ በበደሌ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት በኩል የቀረበውን የጂም ቁሳቁስ (GYM Equipments ግዢ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ህጋዊ የሆኑና መስፈርቱን የሚያሟሉ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የበደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ውስጥ ለሚሰሩ የመንግሥት ሠራተኞች መዝናኛ እና ለጤና አጠባበቅ አገልግሎት የሚውል ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የጂም (GYM) አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ በበደሌ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት በኩል የቀረበውን የጂም ቁሳቁስ (GYM Equipments ግዢ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ህጋዊ የሆኑና መስፈርቱን የሚያሟሉ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
- የእስፖርት እቃዎችንና የጂም ቁሳቁስ (GYM Equipments) ለማቅረብ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የ2017 ዓ.ም የመንግሥት ግብር ከፍሎ ለ2018 በጀት ዓመት ንግድ ፈቃዱን ያደሰና ማቅረብ የሚችል፡፡
- የቫት (ተጨማሪ እሴት ታክስ 15) ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃውን የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያለውና ማስረጃውን የሚችል፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር መዝገብ ላይ የተመዘገበና ማስረጃውን የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) በበደሌ ከተማ ሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1071291641810 ላይ ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በመንግሥት ጨረታ እንዳይሳተፍ ያልተከለከለ ወይም የተከለከለ ከሆነ የተከለከለበትን ጊዜ ገደብ የጨረሰ።
- በዚህ ማስታወቂያ ላይ ከተራ ቁጥር 1 - 4 የተዘረዘሩት መስፈርቶች መኖራቸውን የሚያሳይ በግልጽ የሚታይ አንዳንድ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም በተራ ቁጥር 5 ላይ የተቀመጠው መስፈርት ኦርጂናል በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርገው ከታሸጉ በኋላ በፖስታው ላይ የቴክኒክ ፖስታ በማለት በግልጽ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የጂም እቃዎች (GYM Equipments) ለእያንዳንዱ በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን (specification) መሰረት እያንዳንዱን የሚያቀርቡበትን ዋጋ ቫት (15%) ጨምሮ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ) በመሙላት ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርጎ ከታሸገ በኋላ ፋይናንሻል (የፋይናንስ ፖስታ) በማለት ፖስታው ላይ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
- አንድ ተወዳዳሪ ለአንድ ውድድር ሁለት (2) ፖስታ ማስገባት ያለበት ሲሆን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ያሉበትን ፖስታ ቴክኒክ በማለት እና ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውንና ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ያለበት ፖስታ ላይ ፋይናንሻል በማለት ተለይቶ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለው የቴክኒክም ሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ተወዳድሮ ያሸነፋቸውን የጂም እቃ (GY Equipments) እስh በደሌ ከተማ አስተዳደር በራሱ ወጪ ጭኖ በማምጣት በሚያስፈልግ ሁኔታ በመገጣጠም ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጎ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- በዚሁ መሰረት ህጋዊ የሆነና መስፈርቱን የሚያሟላ ማንኛውም ነጋዴ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ30/1/2018 ዓ.ም ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት መካከል የበደሌ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሠዓት በአካል በመቅረብ የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ የኢትጵያ ብር) በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በደሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል በመንግሥት የሥራ ሰዓት በማምጣት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ስለሚገዙ የጂም ዕቃዎች ሙሉ ማብራሪያ ከነ ፎቶው የሚያሳይ ዝርዝር መግለጫ በሶፍት ኮፒ (በፍላሽ ወይም በቴሌግራም) በመውሰድ ለዋጋ ማቅረቢያ የሚሆን የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በሀርድ ኮፒ (በወረቀት ላይ) የተዘረዘረ በመውሰድ መወዳደር ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ጨረታው በ20/2/2018 ከጠዋቱ በ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4፡30 ሠዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው በቂ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0474450942 በስራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የበደሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
