የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የሱቅ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን በዋናው መስሪያቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
|
ሎት |
የዕቃው አይነት |
ብዛት |
ሱቁ የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
ጨረታ የሚከፈትበት ቦታ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
|
|
የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን ሱቆች |
24 |
አዲስ አበባ |
18/02/2018 ዓ.ም |
4፡00 ጠዋት |
18/02/2018 ዓ.ም |
4፡30 ጠዋት |
አ.አ ዋናው መስሪያ ቤት |
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች (መመሪያዎች) ፡-
- የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ብሎክ 2፣ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግንባር በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
- የጨረታ ሰነድ የዙ ተጫራቾች ለኪራይ የተዘጋጁትን ሱቆች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ለመክፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ሱቆች በሚገኙበት ቦታዎች በአካል በመገኘት ኮርፖሬሽኑ በሚመድበው ሰራተኛ አስጎብኚነት መመልከት ይችላል።
- ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች የሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ከሰነዳቸው ጋር የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል። አሸናፊ ለሆኑትና ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ህጋዊ ባንክ ከሆነ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ሊታሰብላቸው ይችላል ወይም ለተሸነፉት ተመላሽ ይደረጋል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ለሱቅ ኪራይ ቅድሚያ የሶስት ወራት የሚከፍሉ ይሆናል።
- ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በላዩ ላይ ድርጅቶች ከሆኑ ማህተም ያረፈበት፣ ግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ሶስት ፊርማ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቹ ሲወዳደር የሱቆቹን ስፋት እና ዋጋውን በግልጽ መሙላት ይጠበቅበታል። ግልጽ መለኪያ እና ዋጋ ያላስቀመጠ ተወዳዳሪ ከጨረታው ይሰረዛል። ተጫራቾች ከአንድ ሱቅ በላይ መጫረት አይችሉም።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንን በተመለከተ ከላይ በሰንጠረዥ ዋናው መ/ቤት በተገለጸው ቀን እና ሰዓት መሰረት ከጠዋቱ በ4:00 ታሽጎ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:30 በዋናው መ/ቤት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች ካሬ ሜትር ዋጋ በቁጥርና በፊደል ስርዝ ድልዝ የሌለበት ገልጸው በታሸገው ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን ገዥ የሚሆነው የነጠላ ዋጋው ይሆናል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0911622263 ወይም 0911008854 /ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሱቆችን ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ድረስ በአካል በመቅረብ ማየት ይቻላል።
- ተከራዮች ሱቆችን ለጌጣጌጥ፣ ለማዕድን ውጤቶች፣ ለባህላዊ አልባሳት እና ቅርጻቅርጾች መሸጫ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎት የሚከራዩ ይሆናል። ከአልኮሆል መጠጥ ውጭ።
- ተከራዩ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖረው ይገባል።
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
+251-0911622263 ወይም 0911008854
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
