የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ 2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መሳሪያዎችንና ስፔር ፓርት ግዥ፣ ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል ለአንድ አመት ውል ይዞ የሚሰራ ሰርቪስ መኪና ኪራይ፣ የፍሳሽ ቆሻሻ መምጠጫ (ማንሻ) መኪና ኪራይ እና እሳት አደጋ መከላከያ ጥገናና ሙሌት ስራ ከሚመለከታቸው አካላት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ 2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መሳሪያዎችንና ስፔር ፓርት ግዥ፣ ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል ለአንድ አመት ውል ይዞ የሚሰራ ሰርቪስ መኪና ኪራይ፣ የፍሳሽ ቆሻሻ መምጠጫ (ማንሻ) መኪና ኪራይ እና እሳት አደጋ መከላከያ ጥገናና ሙሌት ስራ ከሚመለከታቸው አካላት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል። በመሆኑም በዚህ ጨረታ የሚወዳደሩ ድርጅቶች፡-
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ /TIN CARD/ ሰርቴፊኬት ያላቸው፣
- አጠቃላይ የግዢው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ አቅራቢው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አጠቃላይ ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሆስፒታሉ ዋና ገ/ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ለፍሳሽ ቆሻሻ መምጠጫ (ማንሻ) መኪና ኪራይ ብር 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር ብቻ/ ሲሆን የሌሎች ግዥዎች ማንኛውንም ግብር እና ታክስ ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/ በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ባንክ ጋራንቲ) ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላትና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ፎቅ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 10 / አስር/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡15 ይታሸጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ቀኑ በዓል /ዝግ /ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር
058 3205738/0582220916 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
