የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት አመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የሞተር ሳይክል፤ የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት አመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የሞተር ሳይክል፤ የኤሌክትሮኒክስ እና የፈርኒቸር ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1፡- ሞተር ሳይክል ግዥ
- ሎት 2፡- ኤሌክትሮኒክስ ግዥ
- ሎት 3፡- ፈርኒቸር ግዥ
በመሆኑም፡-
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 70,000 (ሰባ ሺህ)፤ ለሎት ሁለት ብር 85,000 (ሰማኒያ አምስት ሺህ) እና ለሎት ሶስት ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ለእያንዳንዱ ሰነድ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ለየብቻ ከስልጤ ዞን ፋይንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ለያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን ለየብቻ በሚገባ በመሙላት ፋይናንሻል አንድ ኦርጂናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በ21ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 21ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ
ተጫረቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467710586
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
