የባቹማ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በ2018 ዓ/ም በበጀት ዓመቱ የሚሰሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስራዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የባቹማ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በ2018 ዓ/ም በበጀት ዓመቱ የሚሰሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስራዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- Street Light
Location: From Municipality Office to Bachuma Primary Hospital
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫሬቶች የሚከተሱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው ለሚሳተፉ በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ፍቃድ ያላቸው እና በዘርፉ ደረጃ-1 የሆኑ ኮንትራክተሮች መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት ስራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድና የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው እንዲሁም የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የስራውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ በግዥ ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል እንድሁም LED ማብራት ናሙና በስራ ዝርዝር ላይ የተገለጸውን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን 1 ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ከግብር ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቀይቶ በ31ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት የሚከፈት ሆኖ በ31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን 4፡00 ሠዓጥ የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በተጨማሪ የጨረታ ሰነድ ላይ የተቀመጡት ቴክኒካል መመዘኛ መስፈርቶች ጨረታ ማወዳደሪያ አካል ተደርጎ ይወሰዳል።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ማምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው። በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት የግምገማ መስፈርቶች በተጨማሪ ማስታወቂያ ላይ ያሉት መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ የቅድመ ብቃት ግምገማ መስፈርት አካል ሆነው ይቆጠራሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንግድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ የሚከተሉትን አድራሻዎች ይጠቀሙ።
0913312489/0979693597/0916333161
በምዕራብ ኦሞ ዞን የባቹማ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት
