Tender Detail

Tender Details


የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለተቋሙ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የእስቴሸነሪ፣ አላቂ የጽዳት እቃ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህንፃ መሳሪያዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች (በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለተቋሙ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የእስቴሸነሪ፣ አላቂ የጽዳት ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህንፃ መሳሪያዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች (በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንዲችሉ ተጋብዘዋል

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN ያላቸው
  3. የግዥው መጠን ብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  5. የሚገዛው የእስቴሽነሪ እና የህንፃ መሳሪያ እቃዎች ግዥ በሎት (በጥቅል) ሲሆን ሌሎች ግዥዎች በነጠላ ዋጋ ውድድር የሚደረግ ሲሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥን በተመለከተ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በማለት ለየብቻ በተለያዪ ፓስታ በማድረግ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. የእስቴሽነሪ፤ ህንፃ መሳሪያዎች፣ የአላቂ የጽዳት እቃ፣ የፈርኒቸር እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ የር ላይ ከዋለበት ቀን 05/02/2018 . ጀምሮ እስከ 20/02/2018 . ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በተቋሙ ስም በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /../ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በአየር ላይ ከዋለበት/ ቀን 05/02/2018 / ጀምሮ እስከ ቀን 20/02/2018 . ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና /ቤት አደራሽ ወይም ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 20/02/2018 . ከቀኑ 800 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 830 ይከፈታል፣
  11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058222100 በመላ ወይም በስልክ ቁጥር 05832205155/058222110 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፈርማና መህተም ማድረግ አለባቸውበተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

 

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

ባህር ዳር

 

Save Tender