በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ጠ/አዝ RecHREATULU በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ/የጨረታ ቁጥር 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ጠ/አዝ RecHREATULU በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው እቃ/ አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ |
|
ሎት 1 |
አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች |
7,000.00 (ሰባት ሺህ ብር) |
|
ሎት 2 |
አላቂ የጽዳት ዕቃዎች |
3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) |
|
ሎት 3 |
አላቂ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ |
3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) |
|
ሎት 4 |
ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች |
10,000.00 (አስር ሺህ ብር) |
|
ሎት 5 |
የመኪና ዕቃዎችና ጌጣጌጥ |
5,000.00 (አምስት ሺህ ብር |
|
ሎት 6 |
የስፖርት ትጥቅ |
7,000.00 (ሰባት ሺህ ብር) |
|
ሎት 7 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) |
|
ሎት 8 |
የጥናት አገልግሎት |
200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) |
|
ሎት 9 |
የመድረክ ዝግጅት |
3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) |
|
ሎት 10 |
የማስታወቂያ አገልግሎት |
10,000.00 (አስር ሺህ ብር) |
መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የገቢዎች ክሊራንስ ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት ያላቸው።
- በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ምዝገባ ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የሚያስይዙት በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በመ/ቤታችን ስም ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለበት፡፡
ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ፒያሳ/ቅዱስ ጊዮረጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሮክቶሬት ቢሮ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕታ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት።
- መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም።
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል /ለየብቻ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፈርማ በማድረግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 342 ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
- ጥቃቅና አንስተኛ ተጫራቶች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰንዱን በነፃ ለመውሰድ
ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፡፡
ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾቾ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙና /ሳምፕል/ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ፣ ይህ ካለሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ማዘጋጃ ቤት 2ኛ ፎቅ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ 1 ሚኒሊክ አደባባይ /ፒያሳ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118680464 ይደውሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
