Tender Detail

Tender Details


በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ህብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የጥገና እና እድሳት አወዳድረን ማሰራት ይፈልጋል።


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ህብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት 2018 . በጀት ዓመት የጥገና እና እድሳት አወዳድረን ማሰራት ስለምንፈልግ በዚህም መሰረት፡-

  • ሎት1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና
  • ሎት2. በር፣ መስኮት፣ የመብራት መስመር ዝርጋታ፣ የግድግዳ ሶኬት እድሳት ጥገና
  • ሎት3. የቧንቧ መስመር የሽንት ቤት መስመር ጥገና
  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው በመስኩ ህጋዊ ሰነድ እና ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት //አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሆኑና ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ሙሉ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና አድራሻ መፃፍ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል በአራዳ /ከተማ ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት የቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት በቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11 ቀን ከጠዋት 400 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 430 ሰዓት ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት ይሆናል።
  6. መስሪያ ቤቱ በሎት 2 የተጠቀሱ የጥገና ስራዎች በአካል መታችሁ ተቁዋሙ በሚያሳያቸው መሰረት አይታችሁ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባችኋል።
  7. ተጫራቾች ሁሉም የጥገና ስራዎች በአካል መታችሁ ተቁዋሙ በሚያሳያቸው መሰረት አይታችሁ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባችኋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  9. የጨረታ አሸናፊ ከተቋሙ ጋር ውል ለመዋዋል በቅድሚያ የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ አለበት።
  10. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዘርፎች ከራሳቸው እቃ ገዝተው ጥገና የሚያከናውኑ ይሆናል።
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ፒያሳ ከመብራት ኃይል ወደ እሪበከንቱ በሚወስደው መንገድ ጎጀብ ጥርስ ህክምና ጎን

ለበለጠ ማብራሪያና ጥያቄ

ስልክ ቁጥር  09-12-85-03-39/09-11-38-31-11

 

በአራዳ /ከተማ ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት

 

Save Tender