ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የሲሚንቶ ማጓጓዝ እና የውሃ ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፈቲንጎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የሲሚንቶ ማጓጓዝ እና የውሃ ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፈቲንጎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ
|
ሎት |
የዕቃው አይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
የማቅረቢያ ቀን
|
|
1 |
01 |
የሲሚንቶ ማጓጓዝ |
100,000.00 |
አንደ አስፈላጊነቱ |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል፡፡
የተጫራቾች መመሪያ፡-
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የ TIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በ CPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴከኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክከል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
7. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ሰኔ 25 PR 03/2017/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በo5 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ነው::
13. ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡- 058-2-20-48-26/ 058-3-20-25-48 በሩክስ ቁጥራችን 058-2-20-48-30 መጠየቅ ይችላሱ፡፡
የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
