አዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፁትን ያገለገሉ ንብረቶች በሀገር ወስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ያገ/ን/ሽ/ግጨ/004/2018
አዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፁትን ያገለገሉ ንብረቶች በሀገር ወስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው ዕቃ (አገልግሎት) አይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
የጨረታ መዝጊያ ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1 |
ሎት 1 - ያገለገሉ አውቶቡሶች በቁርጥራጭ (SCRAP) መልክ! |
በሚወዳደሩበት የአውቶቡስ መጠን ልክ የመነሻ ዋጋ 20% |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት |
|
2 |
ሎት 2 - ያገለገሉ የተማሪ አውቶቡስና የዳፍ ተሽከርካሪ ጎማዎች |
ለውድድር የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10% |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት |
|
3 |
ሎት3-ያገለገሉ ቁርጥራጭ አልሙኒየም (scraped Almunim) |
ለውድድር የቀረበውን የጠቅላላ ዋጋ 10% |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት |
|
4 |
ሎት 4 - ያገለገሉ ጋዜጣዎች |
ለውድድር የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10% |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት |
ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት |
ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ሀጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው::
2. ተጫራቾች 22 በሚገኘው እየሩስ ህንፃ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ደርጅት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡ oo ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቃሊቲ ቅ/ፅ/ቤት፣ የካ ቅ/ፅ/ቤት፣ ሸጎሌ ቅ/ፅ/ቤት፣ ሰሚት ቅ/ፅ/ቤት፣ መካኒሳ ቅ/ፅ/ቤት እና በዋና መ/ቤት በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለሎት አንድ በሚወዳደሩበት የአውቶቡስ መጠን ልከ የመነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ)እና ከሎት ሁለት እስከ ሎት አራት ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (አስርበመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
5. የጨረታ ሳጥኑ ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሃያ ሁለት እየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር08
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-6-66-33-67 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
