በደ/ኢ/ክ/መንግስት በጎፋ ዞን የበቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በጎፋ ዞን የበቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡-
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
- ሞተር ሳይክሎችን፣
- ጽዳት ዕቃዎችና ጽ/መሣሪያን፣
- የፋብሪካ ውጤቶች፣
- ፈርኒቸሮችን፣
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፤
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው፣
- ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወርቀት ማቅረብ የምትችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ለኤሌክትሮኒክስ 10,000 ብር፣ ለሞተር ሳይክሎች 10,000፣ ለጽዳት ዕቃዎችና ጽ/መሣሪዎች 10,000 ብር፣ ለፋብሪካ ውጤቶች 10,000 ብር እና ለፈርኒቸሮች 10,000 ብር ለየብቻው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሳ ከ1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት በቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.3 ማስገዛት ይቻላል፣
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 ለእያንዳንዱ ዕቃ ለየ ብቻ በመክፈል ከበቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ያገኛሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ እስከ በቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል አምጥቶ ማስረከብ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከማየት አያግድም፤
- አሸናፊ ድርጅቶች ከአሸነፈበት ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዣ ሲያሲዙ የጨረታ ማስከበሪያው ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ጽ/ቤቱ ግዥውን ሲፈጸም ከጠቅላላ ዕቃ ግዥ የዕቃው 20% የመጨመር ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ - የስ.ቁ 0916517844/0982423551 ይደውሉ፡፡
በደ/ኢ/ክ/መንግስት በጎፋ ዞን የበቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
