የ404ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት አመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የ404ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት አመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ሰርተፍኬት፣ ግብር ስለመክፈሉና ጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠ ማስረጃ/ በየወሩ ቫት ለመንግስት ገቢ ያደረገበት ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት አሶሳ 404ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ዴስክ ቢሮ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት ከጠቅላላ ዋጋ 2% በኋላ ላይ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በተገለፀው መሰረት በባንክ የተረጋገጠ CPO በዕለቱ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለተለያዩ አይነት የሲቪል ሰራተኛ አልባሳት ብር 8,000.00
- የተለያዩ አይነት የቢሮ የፅህፈት እቃዎች ብር 31,100.00
- የተለያዩ አይነት የትምህርት መርጃ ዕቃዎች ብር 20,880.00
- ለተለያዩ አይነት ጥራጥሬ እና የፋብሪካ ውጤቶች, 111,075.48
- የተለያዩ አይነት የፅዳት ዕቃዎች ብር 107,238.08
- የተለያዩ አይነት የቀላል ተሽከሪካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 10,000.00
- ጨረታው ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በዚሁ ዕለት ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡45 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ404ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ዳቡስ ካምብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር / 0910212914 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የ404ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ
