Tender Detail

Tender Details


የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በየሎቱ ተዘርዝረው የተገለፁትን የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ጥር 2/2018

 

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በየሎቱ ተዘርዝረው የተገለፁትን:-

  • ሎት-1 የህምና እቃ ግዢ
  • ሎት-2 ለምግብ ማደራጃ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ግዢ
  • ሎት-3 የህክምና እቃ ጥገናና ሰርቪስ
  • ሎት-4 የኤሌክትሮኒ እቃዎች ጥገናና ሰርቪስ
  • ሎት-5 የፕሪንተር ቶነር ግዢ

ከላይ የተዘረዘሩ የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የተጫራቾች መመሪያ በር አለባቸው፡-

  1. ተጫራ በዘርፉ የተሰማሩበትን የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ እና ከገቢዎች የታደሰ የመጫረቻ ፈቃድ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ሆኖ ሁሉንም የተጠየቁ ማስረጃዎች በግልጽ የሚታይና የሚነበብ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራ የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ) ብቻ በመፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅዳሜ፣ ዕሁድ የበዓል ቀናትን ሳይጨምር በሚቆጠር እስከ 10ኛው ቀን 10:45 ሰአት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ፖስታዎቹ ላይ ከውጭ ሎቶቹን በመፃፍና ማህተም በማድረግ፤ በየሎቱ ለየብቻ ተለይተው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ኦርጂናል የማይመለስ ኮፒውን 11ኛው ቀን 400 ድረስ በመለየት የሚቀርብ ሆኖ ጨረታው በሚከፈትበት እለት ወይም እስከ ግዢ ፍል በሚገኘው የጨረታ ቡድኑ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ (በዚሁ ዕለት) 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ቡድኑ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሳምፕል፤ ካታሎማ ይቅረብ በተባለው ላይ ያቀርባሉ፤ ስፔስፊኪሽን ያላቸውን በጥንቃቄ በማየት መጫረት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት-1 ሎት-2 ሎት -3 ሎት-4ሎት-5 ለእያንዳንዱ 50,000 (ሃምሳ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የዋስትና ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተቀመጠው ሰነድ መሰረት ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ በመለየት በሆስፒታሉ የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራ በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሃሳብ ካላቸው ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሆስፒታሉ የግዢና እቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት የስራ ክፍል በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።
  10. የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይተው ውል እስኪፈጸም ድረስ እንደተያዘ ይቆያል።
  11. ተጫራ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባለው የቅሬታ ማቅረቢያ የሚታይበትን ቀን ጨምሮ 7 ቀን በኋላ ሸናፊዎች አዋርድ ወስደው 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ በማስያዝ 3 ቀን ውስጥ ውል ተዋውለው በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች ስፔስፊኬሽኑ እና ሳምፕል የቀረበባቸውን በሳምፕሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
  13. የጨረታውን 20% መጨመርና 20% መቀነስ ይቻላል፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችለው በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ብቻ ሲሆን በአነስተኛና ጥቃቅን ንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማራችሁ የንግድ ስራ መለያ ኮድ በደብዳቤ ላይ በመግለፅ ጨረታውን መሳተፍ የሚችሉ ይሆናል፡፡
  15. ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

መረጃ - በስል ቁጥር 011-515 -02-42 በመደወል መረዳት ይችላሉ ፡፡

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቂርቆስ /ከተማ ፍል ውሀ አጠገብ ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

 

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል

Save Tender