የጉላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለክፍለ ከተማው ማዘጋጀ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ገልባጭ መኪናዎች፣ ሎደር፤ ኤክስካቫተር፣ ዶዘር D8R፣ ግሬደር እና ሩሎ፣ መኪናዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለክፍለ ከተማው ማዘጋጀ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ገልባጭ መኪናዎች፣ ሎደር፤ ኤክስካቫተር፣ ዶዘር D8R፣ ግሬደር እና ሩሎ፣ መኪናዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደስ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ ወይም ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺ አምስት መቶ ብር) ወደ ሰንቄ ባንክ አካውንት ቁጥር 1054490110216 ላይ ገቢ በማድረግ ወደ ክፍለ ከተማው ገቢ ጽ/ቤት ወደ ደረሰኝ ማስቀየር ከክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ የስራ ሂደት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO በገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚያከራዩበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሽግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉትን ማሽነሪ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ወይም የኪራይ ውል ከሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (15%) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ነዳጅንና ሌሎች ውጭዎችን በአከራይ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን አገልግሎቶች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ/ሥራ የሚሰራበት ቦታ/ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱ የሚሸጥ ሲሆን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የመ/ቤቱ አድራሻ ከአዲስ አበባ 20 ኪሜ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ አጠራር ኬንተሪ ዋንጋሪ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ ነው።
የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
