የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የተማሪዎች ዴስክ እና ጥቁር ሰሌዳ በጨረታ መለያ ቁጥር ጋም-ትም-ዕቃ-መደ-ዴስከ-01-2018 እንዲሁም ከEETOL በተገኘ በጀት ለ2018 ትምህርት ዘመን በኢታንግ ልዩ ወረዳ ለሚገኙ ሦስት የስደተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (ለቴርኮዲ፣ ጉኜል እና ኩሌ) ለመምህራንና ለአስተዳደር ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በግዥ መለያ ቁጥር GaREB-GEQIP-E-Non-con-EETOL-2017-3 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ

|
|
የዕቃ ዓይነት |
መለያ ቁጥር |
የበጀት ምንጭ |
የጨረታ ማስከበሪ |
|
1 |
የተማሪዎች ዴስክ እና ጥቁር ሰሌዳ |
ጋም ትም-ዕቃ መደ-ዴስክ-01-2018 |
መደበኛ
|
105,000
|
|
2 |
የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ |
GAREB GEQIP-E-Non-con-EE-TOL-2018-1 |
EETOL
|
110,000
|
ቢሮው ህጋዊ አሰራርን በተከተለ የጨረታ ሂደት ተጫራቾችን አወዳድሮ ዴስኮችን እና ጥቁር ሠሌዳ ለማሰራት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ተጫራቾች:-
1. በመስኩ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት /ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (የጥሬ ገንዘብ ከፍያ ማዘዣ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ብቻ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. የብቃት መስፈርቶችን በተመለከተ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ የተጠየቁ ህጋዊነትን የሚያመለከቱ የሰነድ ቅጅ እና ከስራው ጋር የተያያዙ ሰነዶች ከጨረታው መልስ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ተከታታይ ቀናቶች የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በትምህርት ቢሮ ቁጥር 20 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንስ ዶክመንት ዋናና 1 ኮፒ አድርገው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0475510136 / 0475511236 / 0475511477
የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ትምህርት ቢሮ