ፀሐይ ባንክ አ.ማ የተለያዩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ፀባ/06/2025-26
ፀሐይ ባንክ አ.ማ የተለያዩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች መወዳደር ይችላል።
|
የተሽከርካሪዎቹ ዝርዝር መረጃ |
||
|
ተ.ቁ |
የሞዴሉ አይነት |
ብዛት |
|
1 |
Hyundai Tucson |
05 |
|
2 |
Eicher-3008G |
02 |
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎች በቅሎቤት አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም የጭነት መኪናዎቹን ደግሞ ቃሊቲ የፀሐይ ኢንሹራንስ ሪከቨሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ከህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ3፡00-5፡30 ከሰዓት ከ8፡00-10፡30 መመልከት ይችላሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጥቅምት 23 ቀን 2018 እስከ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ፀሐይ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ላይ በተከፈተው አካውንት ቅጥር 1000033657 ገቢ በማድረግ የጨረታውን ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንያንዱ ተሽከርካሪዎች በተናጥል የመነሻ ዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በፀሐይ ባንክ ስም በማዘጋጀት ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ከአንድ በላይ ተሸከርካሪ መጫረትና መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው የፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለዉ የዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ዋናዉንና ኮፒዉን በተለያዩ ፖስታ በማድረግና ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ ዉስጥ አድርገው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉትን ተሸከርካሪ ሙሉ ክፍያ በመክፈልና የአሸናፊነት መግለጫ ደብዳቤ ከባንኩ ካገኙበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር በ10 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ በማድረግ መኪናውን መረከብ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ያልከፈለ ተጫራች ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
- በጨረታው ተሳትፈው ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ለስም ማዛወሪያና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎችን በሙሉ የሚሸፍን ይሆናል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0114705613/ 0114705055 ይደውሉ።
