የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለእንዳልካቸው ንጋቱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የተመሰረተ የዋስትና መብት አዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
የዝግ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለእንዳልካቸው ንጋቱ ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የተመሰረተ የዋስትና መብት አዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው (የመያዣ ሰጪው) ስም |
የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
እንዳልካቸው ንጋቱ |
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ፣ ጆጎ ጉዴዶ ቀበሌ ውስጥ 6000 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ የወተት ማቀነባበሪያ ማሽኖች እና 6 (ስድስት) ተሽከርካሪዎች |
46,286,021.48 |
1ኛ |
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ታህሳስ 03 ቀን 2018 ጠዋት 4፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ-
- ተጫራቾቹ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የባንክ ክፍያ ማስያዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾቹ ሰነዱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት በመውሰድ የሚገዙትን ንብረት፤ የሚገዙበትን ዋጋ፤ ስምና አድራሻ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ንብረቱን በብድር መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የባንኩን የብድር መስፈርት ማሟላትና ንብረቱን የሚገዙበት ዋጋ፣ ስለ ቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ሁኔታ፣ ለቀሪው የንብረት ዋጋ አከፋፈል ከሚገዙት ንብረት በተጨማሪ የሚያቀርቡት የመያዣ ዓይነት፣ ግምትና የሚገኝበት ቦታ በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን ሲ.ፒ.አ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ጥሬ ገንዘብ (Cash) በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡
- የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት ናፍራን ሕንፃ 3ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-212-04-17 ላይ መደወል እንዲሁም ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
