Tender Detail

Tender Details

  • Company ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-126-78-16
  • Website
  • Deadline21 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-11-21 00:00:00
  • Categories Cloth And Shoes

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ለ2018 በጀት ዓመት ለሠራተኞች የደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውሉ ብትን ጨርቅ፣ የወንድ ጫማ፣ የሴት ጫማ፣ ሴፍቲ ጫማ፣ ሽሚዝ፣ የዝናብ ልብስ፣ የሱፍ ካፖርት፣ የጽዳት ሽርጥ፣ ቱታ እና ልዩ ልዩ የደንብ ልብሶችን በግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ /001/2018

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት 2018 በጀት ዓመት ለሠራተኞች የደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውሉ ብትን ጨርቅ፣ የወንድ ጫማ፣ የሴት ጫማ፣ ሴፍቲ ጫማ፣ ሽሚዝ፣ የዝናብ ልብስ፣ የሱፍ ካፖርት፣ የጽዳት ሽርጥ፣ ቱታ እና ልዩ ልዩ የደንብ ልብሶችን በግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስሰዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይታትሞ ከመጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ህዳር 12 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ለዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈልና በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ዋናውን ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት /ቤት ውስጥ የተደራጁ ህጋዊ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፤ ከአደራጃቸው ተቋም የሚያቀርቡት የድጋፍ ደብዳቤ ውስጥ መካተት ያለባቸው ሁኔታዎች የሚወዳደሩበትን ተቋም ስም፣ የሚወዳደርበትን የግዥ ዓይነት፣ የጨረታ ቁጥር እና የጨረታ ማስከበሪያውን የገንዘብ መጠን በግልጽ በአሃዝና በፊደል የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው::

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን የቴከኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ለየብቻው በፖስታ በማድረግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ ከሴት ታከስ የምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስከርወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከሪላንስ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሬጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል ሚገባበት ቅፅ ሞልታችሁ ማህተምና ፊርማ አድርጋችሁ የመጫረቻ ለነዶቻችሁን አሟልታችሁ በማቅረብና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ህዳር 12 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ስዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው::

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ህዳር 12 ቀን 2018 ከጠዋቱ 430 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና /ቤት ይከፈታል። አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት

Save Tender