በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሁሉም ባለበጀት መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሎት:- 1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት፡- 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት፡-3 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት፡- 4. ፈርኒቸር ዕቃዎችን እና ሎት፡-5. የመኪና ስፔር ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሁሉም ባለበጀት መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሎት:- 1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት፡- 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት፡-3 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት፡- 4. ፈርኒቸር ዕቃዎችን እና ሎት፡-5. የመኪና ስፔር ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ግብር ከፍይ መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የእቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 05/03/2018 ዓም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ፤ በዚሁ ቀን 4፡00 ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻው ቀን የበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በዚሁ በተባለው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-240-58-69 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የጊምባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
