በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል በግቢው ውስጥ የሬስቶራንት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን 164.3 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን ንግድ ቤት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ለ3 ዓመት ማከራየት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የስፖርት ባርና ሬስቶራንት ጨረታ ቁጥር 05/2018ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል በግቢው ውስጥ የሬስቶራንት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን 164.3 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን ንግድ ቤት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ለ3 ዓመት ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟሉ በማወዳደር ተጫራቾችን ወደ ሥራ ማስገባት ይፈልጋል፦
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸው የሚገልፅ ትክከለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የህጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ ከአስ/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር ከፍለው መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የዝዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ንግድ ቤቱን ለምን አገልግሎት እንደሚፈልጉ ገልጸው በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ውስጥ በዝርዝር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስም የተሰራ ሲ.ፒ.ኦ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው ለሚመጡ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን 8:00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ከተባለው ቀንና ሰአት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ አጠገብ ወይንም ከመድኃኔ ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከሚገኘው አደባባይ ወደ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው አስፋልት መንገድ በስተግራ 100 ሜትር ገባ ብሎ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማእከል
