አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሥራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን፡- ቦሌ ክ/ከተማ ቡልቡላ ሳይት ብሎከ 8 የቤት ቁጥር 204 እና 205 የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ የተሻለ ዋጋ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የንግድ ቤት ኪራይ 1/2018
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል እቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሥራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን፡- ቦሌ ክ/ከተማ ቡልቡላ ሳይት ብሎከ 8 የቤት ቁጥር 204 እና 205 የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ የተሻለ ዋጋ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ለማከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል፡፡
1. ተጫራቾች ተወዳድረው ባሸነፉበት የንግድ ቤት ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ለማውጣት፥ ቤቱን ተከትሎ ማህበራዊ ወጪዎች ማለትም የተጠቀሙበትን የውሃ እና የመብራት ፍጆታ ወጪዎችን ለመከፈል ፈቃደኛ የሆኑ እና የነዋሪዎችን ሰላም የማያደፈርስ ሥራ ለመሥራት ፍቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የንግድ ቤት የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 26/03/2018 ዓ.ም የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንፃ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ ኢማ ዋና መሥሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ፋይናሽያል ሰነድ ኦርጅናል እናኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 26/03/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው በ26/03/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ ኢማ ዋና መ/ቤት ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
6 ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተ ከርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ሕንፃ ጎን
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-1-26-38-88 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ
