የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የማንዋል ህትመት አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የህትመት አገልግሎቱን አታሚ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል።
የምርጫ ማንዋል የህትመት
አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: NEBE/NCB/07/2018
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የማንዋል ህትመት አገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የህትመት አገልግሎቱን አታሚ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 200.00 (ብር ሁለት መቶ) በመከፈል ከቦርዱ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 107 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንሽልና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት የግብር ከሊራንስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ነው፡፡
6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።
7. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት 300,000.00 (ብር ሶስት መቶ ሺ) በቅድመ ሁኔታ ላይባልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በሲፒአ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ቦርዱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
9. ጨረታው ህዳር 29 ቀን 2018 ከሰዓት በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ላይተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦርዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
10. በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
11. ቦርዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
12. ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አድራሻችን፡-ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር +251 115153468
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
