Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማእከል
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም መድኃኒያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤ ትልቁ አደባባይ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተግራ ገባ ብሎ : አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline28 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-11-28 00:00:00
  • Categories Audit Service

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ምክር ቤት የ2016-2017 ዓ/ም የሂሳብ ሰነድ ኦዲት ለማስደረግ በማስፈለጉ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ አገልግሎቱን ማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም ከታች በዝርዝር የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ ።


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ምክር ቤት የ2016-2017 ዓ/ም የሂሳብ ሰነድ ኦዲት ለማስደረግ በማስፈለጉ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ አገልግሎቱን ማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም ከታች በዝርዝር የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ ።

1. የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል

2. የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል

3. የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል

4. በመንግስት ግዥ አገልግሎት ሰጪነት መመዝገባቸውን የሚገልጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል

5. የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስም 30,000 / ሰላሳ ሺህ ብር / ሰ.ፒ.ኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 05 /አምስት/ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ / ለሰነዱ በመክፈል ከቢሮ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይቻላል።

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናንሺያል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ በታሸገ

ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 05/ አምስት / ተከታታይ የስራ

አዲስ አበባ አስተዳደርን በመንግስት ግዥ አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።

ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ 6 / ስድስት/ኛው የስራ ቀን በ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ

ይከፈታል ፡

የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒ ኦ. ከ 7ቀን በኋላ ተመላሽ ይደረጋል

የጨረታ አሸናፊው በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጹሁፍ በተገለጸ በ7 /ሰባት / ቀናት በኃላ አስፈላጊውን የውል ማስረከቢያ ገንዘብ በማስያዝ ውል መዋዋል አለበት ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲ.ፒ.ኦ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል ። ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው ።

ተጨማሪ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 0118-12078 አድራሻ 1- ቦሌ ፍላሚንጎ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አጠገብ አዲስ አበባ ባህልና ኪነ ጥበባት ቢሮ ያለበት ህንጻ 4ኛ ፎቅ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

Save Tender