የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 08/2018
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ምድብ -1፡ RHS, SHS & Angle Irons
ምድብ -2: Various Electromechanical materials & consumables
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች አግባብነት ያለው የዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት (VAT)፤ የግብር ከፋይ መለያ የምስክር ወረቀት (TIN)፤ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከግብርና ታክስ ሰብሳቢ መ/ቤቶች የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለምድብ-1፡ ብር 50,000.00፤ እና ለምድብ-2፡ ብር 50,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ የመወዳደሪያ የመጫረቻ ሰነዶች በታሸጉ ኢንቨሎፖች በአንድ ኦሪጂናልና በአንድ ኮፒ እስከ 22/3/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ቀን 22/3/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱ ምድብ የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 602 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር 011-551-32 88 ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
