ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ጎማዎች፣ የኤክስካቫተር አካፋዎች፣ ጃክሀመሮች፣ የሪቬት መምቻ ማሽን፣ የሆዝ መጭመቂያ ማሽን፣ ፕረስ ማሽን፣ የቸርኬ ማውጫ ማሽን፣ ፍሎር ጃክ፣ ቶርክ ሬንች፣ ላሜራ መቁረጫ ማሽን፣ የቸርኬ ባላንስ ማሽን፣ የጎማ መፍቻ በኤሌክትሪክ የሚሰራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ዘመን/ማሽን 04/2018
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ጎማዎች፣ የኤክስካቫተር አካፋዎች፣ ጃክሀመሮች፣ የሪቬት መምቻ ማሽን፣ የሆዝ መጭመቂያ ማሽን፣ ፕረስ ማሽን፣ የቸርኬ ማውጫ ማሽን፣ ፍሎር ጃክ፣ ቶርክ ሬንች፣ ላሜራ መቁረጫ ማሽን፣ የቸርኬ ባላንስ ማሽን፣ የጎማ መፍቻ በኤሌክትሪክ የሚሰራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እቤት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
- የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም /unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል የጨረታ ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናት በመቁጠር) ድረስ ብቻ ዘመን ኮንስትራክሽን የማሽ/ተሽ/መ/ግዥና አቅ/ኬዝ ቲም ቢሮ (ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በተራ ቁጥር 4 በተገለጸው ቦታ በ8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል። የመዝጊያና መክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚያኑ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።
- ዝርዝር የጨረታ መመሪያውን እና የውል ይዘቱን እንዲሁም የሚገዙትን እቃዎችና አገልግሎቶች፣ ዝርዝር ቴክኒካል መገምገሚያዎች በሙሉ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለበት።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተመጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር:- 058-3205185/0918784490/0927605599
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
