የጨረታ መለያ ቁጥር 06/2018 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 06/2018 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥው ዓይነት
ሎት 1. የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
ሎት 2. የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫዎች
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀዉ መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በስራው ዘርፍ ቀጥተኛ እና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ/ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በመሙላት በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
4. ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 5000 አምስት ሺህ ብር) በሲፒኦ CPO ብቻ በማስያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሪጅን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብርብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል። ካልተገለጸ ግን ቫትን እንዳካተተ ደርጎ ይወሰዳል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት ኮፒ እና ኦርጂናል በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት በተገለፀው ቀን ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፀው መሰረት ናሙና እንዲቀርብ በተጠየቁት ዕቃዎች ላይጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ ላይ በወጣ በ 6ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. ሪጅን ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ሀዋሳ ቤተሰብ መምሪያ አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 046-221-43-17/046-221-41-40/0913733812
የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት
