የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያለትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም ሎት 1፡- የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽ በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮሪደር ልማት ቄራ አትከልት ተራ ፣ 22 አካባቢ ፣ ካዛንችስ ፣ ፍላሚንጎ ፣ ኮርያ ፓርh ውስጥ ፣ ልደታ አካባቢ ፣መገናኛ፤ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ስላሴ አካባቢ፣ አቃቂ አካባቢ፣ ላፍቶ አደባባይ ፣ አራት ኪሎ ማተሚያ አካባቢ ፣ ፒያሳ አካባቢ ፣ ሾላ አካባቢ ፣ ሆላንድ ኢንባሲ አካባቢ ፣ ሸጎሌ አካባቢ ፣ ለቡ ፣ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም አካባቢ፣ ስድስት ኪሎ አካባቢ ፣ ሰሚት ፣ ጎሮ ፣ፊጋ አካባቢ ፣ ገርጂ ኦቪድ ሪል ስቴት አካባቢ ፣ ቡልቡላ መንገድ ፣ በአራት ኪሎ ፕላዛ (Underpass) ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እና ቦታዎች ለማከራየት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራጮች ተጋብዘዋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 49
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያለትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም ሎት 1፡- የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽ በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮሪደር ልማት ቄራ አትከልት ተራ ፣ 22 አካባቢ ፣ ካዛንችስ ፣ ፍላሚንጎ ፣ ኮርያ ፓርክ ውስጥ ፣ ልደታ አካባቢ ፣መገናኛ፤ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ስላሴ አካባቢ፣ አቃቂ አካባቢ፣ ላፍቶ አደባባይ ፣ አራት ኪሎ ማተሚያ አካባቢ ፣ ፒያሳ አካባቢ ፣ ሾላ አካባቢ ፣ ሆላንድ ኢንባሲ አካባቢ ፣ ሸጎሌ አካባቢ ፣ ለቡ ፣ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም አካባቢ፣ ስድስት ኪሎ አካባቢ ፣ ሰሚት ፣ ጎሮ ፣ፊጋ አካባቢ ፣ ገርጂ ኦቪድ ሪል ስቴት አካባቢ ፣ ቡልቡላ መንገድ ፣ በአራት ኪሎ ፕላዛ (Underpass) ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እና ቦታዎች ለማከራየት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራጮች ተጋብዘዋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት፡፡
2. ፓርኮቹ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነና የተቋማችን ጋር ውል ገብቶ በገበያ ጥናት እና የመነሻ ዋጋ መሰረት ተወዳድረው አስፈላጊውን ከፍያ የሚከፍልና በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚችል፡፡
3. በግቢ ያሉ ፋውንቴኖችንና ፤ መናፈሻዎችን ፣ የመጸዳጃ ቤቶችን ፣ የጽዳት ፣ የጥበቃ ፣የተለያዩ ጥገናዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በመሆን ማስጠገን ፣ መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደር የሚችል።
4. ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ፡፡
5. ኮርፖሬሽኑና የከተማ አስተዳደሩ በሚወጣው የስራ ሰአት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ፣ በአላትን እንዲሁም ምሽትን ጨምሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል፡፡
6. አሸናፊነት ከታወቀ በኃላና ውል ከወሰደ በኃላ በ3 ቀን ውስጥ ስራ መጀመር የሚችል፡፡
7. ስታንዳርዱን የጠበቀ እና የኮሪደር ልማቱን የሚመጥን እቃዎችን ይዞ መግባት የሚችል፡፡
8. ከተቻለ በሬስቶራንት፡ በካፌ እና ህዝብ መዝናኛ ፓርክ ላይ ልምድ ያለውና መረጃ ማቅረብ የሚችል
9. ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ሎቶች 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንከ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋስ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11:30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት እና ቴክኒካል ዶክመንት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኃላ ካለው 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋስ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ በግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
13.የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
14, ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
15, ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 0777619010 /0915862636 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን
