የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ በፈተና በጀት እና በአለም ምግብ ፕሮግራም በጀት በመጠቀም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም በሥራ መስክ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም/ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ በፈተና በጀት እና በአለም ምግብ ፕሮግራም በጀት በመጠቀም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ሀ. ለፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ስራ የሚያገለግል ማለትም
- የስካነር ማሽን ----------------------------------------------------- ብዛት 2
- የፕሪንተር ማሽን -------------------------------------------------- ብዛት 4
- የላፕቶፕ ኮምፒተር ----------------------------------------------- ብዛት 2
- የኤሊ ሲዲ ፕሮጀክተር -------------------------------------------- ብዛት 2
- የብሎወር --------------------------------------------------------- ብዛት 1
- የስካነር ማሽን ስካን ኤይድ ኪት ------------------------------------ ብዛት 1
- የኤች ፕ ሌዘርጀት ኢንተርፕራይስ ኤም611 ስሪየስ ---------------- ብዛት 1
- የፈተና ማስቀመጫ ካዝና ------------------------------------------ ብዛት 1
ለ. በአለም ምግብ ፕሮግራም በጀት
- የሞተር ሳይክል --------------------------------------------------- ብዛት 2
- ጋላክሲ ታብሌት -------------------------------------------------- ብዛት 3
እነዚህን ዕታዎችን ግዥ ለመፈጸም በሥራ መስክ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃዳቸውንና የምዝገባ ሰርተፍኬታቸውን ያሳደሱ በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፣ የዘመኑን የግብር ግዴታውን የተወጣ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበት፣ መረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች በትምህርት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱን ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- የፋይናንሻል ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ ለየብቻ አሽጎ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮ ቁጥር 8 ለዚህ በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የሚገልጽ 1ኛ. ለፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ስራ የሚያገለግል የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የገንዘብ መጠን ብር 75,000.00 /ሰባ አምስት ሺህ ብር/ ጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 2ኛ. ለአለም ምግብ ፕሮግራም ለስራ የሚያገለግል የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የገንዘብ መጠን ብር 37,000.00 /ሰላሳ ሰባት ሺህ ብር/ ጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ የስራ ቀን ላይ በተባለው ቦታና ሰዓት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0467752359/0916863055 መጠየቅ ይችላሉ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትም /ቢሮ/ ጅንካ
