Tender Detail

Tender Details

  • Company Hibir Construction Corporation (ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
  • Address ባህር ዳር ከተማ አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ዋና መ/ቤት ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-320-35-76
  • Websitehttps://arwe.et/
  • Deadline25 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-25 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing , Finance

የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሳብ በIFRS ሂሳቡን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።


 

የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት ግዥ

ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን 2017 በጀት ዓመት ሂሳብ IFRS ሂሳቡን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል። በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል።

  1. የድርጅቱን ሂሳብ IFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፤
  2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፣
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መሥሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ የሚሰጡ ከሆነ)
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፣
  5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመግዛት መጫረት ይቻላል።
  6. ከብር (200,000.00) /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆን ግዥ ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ 2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያ ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ውስጥ ዋናው ቢሮ ግዥ ክፍል ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ውጪ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20ኛው ቀን፤ ከቀኑ 800 ዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 830 ዓት በድርጅቱ ግዥ ከፍል ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 20ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን 830 ይከፈታል።
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡- 058 320 3576 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል።

 

ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

/ዳር

 

Save Tender