የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በዓለም ህጻናት መርጃ ድርጅት /UNICEF/በተመደበ ገንዘብ ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች! ኤልሲዲ ፕሮጀከተር፣ ፕሪንተር፣ ሄድፎን፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች ፣ ሼልፎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን እንዲሁም ለመምህራንና ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ እስከርቢቶ፣ ደብተር፣ ቦርሳና ጋውን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EB/EMAS/014/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በዓለም ህጻናት መርጃ ድርጅት /UNICEF/በተመደበ ገንዘብ ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች! ኤልሲዲ ፕሮጀከተር፣ ፕሪንተር፣ ሄድፎን፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች ፣ ሼልፎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን እንዲሁም ለመምህራንና ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ እስከርቢቶ፣ ደብተር፣ ቦርሳና ጋውን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊና በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ለልዩ ፍላጎት ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ኤልሲዲ ፕሮጀከተር፣ ፕሪንተር፣ ሄድፎን፣ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች ፣ ሼልፎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎችን እንዲሁም ለመምህራንና ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ እስከርቢቶ፣ ደብተር፣ ቦርሳና ጋውን የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ (Specifcation) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600.00 /ስድስት መቶ ብር/ በመከፈል ቢሮ ቁጥር103 ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በጨረታ ሰነዱ ከተራ ቁጥር 9.1.11 እሰከ 9.3.1.4 በተገለጸው መሠረት ሲሆን ይህም በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሐሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ግብዓት ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትርበስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ ማስገባት የሚቻለው እስከ ጥዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
8. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10, በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ