Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 29/2018

 

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ //ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ታህሳስ 02 ቀን 2018 . ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን።

በመሆኑም

  1. በተሽከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
  2. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  3. በጨረታው ላይ የተሽከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
  4. ተጫራቾች የተሽከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ታህሳስ 02 ቀን 2018 . ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ// ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
  5. በዕቃና ተሽከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ወይም ተሽከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ//ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

 

.

የቅ//ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

. ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት

የእቃ ግልፅ

እስከ 07/04/2018

08/04/2018. 345 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል።

የተሽከርካሪ ግልጽ

እስከ 07/04/2018

08/04/2018 . 345 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል።

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡-አ. ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
  2. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
  4. ከላይ በተ/ 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  5. /ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩ - 011 470 85 - 03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ / በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

 

በጉምክ ኮሚሽን . ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት

 

Save Tender

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ለብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

READ MORE
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት መጠቀሚያ የሚሆን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽ...

READ MORE