ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች፣ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ስርገት መከላከያ፣ የተለያዩ ፓምፖች እና የተለያዩ የውሃ ታንከሮች አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል (AC System) አቅርቦት እና ገጠማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 19/2018፤ 20/2018 እና 21/2018
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት
- ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት ጨረታ ቁጥር 19/2018
- ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ስርገት መከላከያ፣ የተለያዩ ፓምፖች እና የተለያዩ የውሃ ታንከሮች አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ጨረታ ቁጥር 20/2018
- የኤሌክትሮ መካኒካል (AC System) አቅርቦት እና ገጠማ ጨረታ ቁጥር 21/2018 ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም እና ሌሎች ቴክኒካል ዶክመንቶች ማቅረብ አለበት፤ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
- የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ በባ/ዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክ/ከ ዋናው አስፓልት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው ዋናው ቢሮ አንደኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል። 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዕለቱ 8፡00 ላይ ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ዉድድሩ በሎት/በምድብ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት/ምድብ ለተጠየቁ የሥራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት። ነገር ግን ለኮርፖሬሽኑ ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ከታመነበት በግዥ መመሪያው መሠረት ውድድሩን በነጠላ ዋጋ በማወዳደር ዝቅተኛ የሆነውን በመምረጥ ግዥ ሊፈፀም ይችላል።
- የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ 45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር
ባህር ዳር 058-218-0538 /09-21-25-89-20/0918716616
አዲስ አበባ ማስተባበሪያ፡- ስልክ ቁጥር 01112655338
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
