Tender Detail

Tender Details


የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተለያየ መንገድ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ እወጋገድ መመሪያ ቁጥር167/2012 እንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 1 የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች ፣ የመኪና እና የሞተር ሳይከል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ላይከሎች፣ቤንዚንና ናፍጣ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር-18/2018

የሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተለያየ መንገድ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ እወጋገድ መመሪያ ቁጥር167/2012 እንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ የኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 1 የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይከል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ላይከሎች፣ቤንዚንና ናፍጣ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝርከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋርበዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም፡፡

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 200 እስከ 600 ከሰዓት 700 እስከ 1100 ሰዓት፣ ቅዳሜ 200 እስከ 600 ሰዓት ድረስ በቅ//ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት በተጫራቹ ስም መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላከ የጨረታ ሰነድ ባለበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል፡፡

3 ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩከ //ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የተመሰከረለትን CPO በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ለሀራጅ, ጨረታ ለመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ብር500,000(አምስት መቶ ሺህ) (CPO) ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት

የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 405 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ///ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ሂደቱ ካለቀ io ደቂቃ በኋላ የሀራጅ ጨረታው የሚጀምር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የስራ ቀናት ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል፡፡

5.ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ከፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክበመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ መቅረብ አለባቸው:: ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ //ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፡፡

6 ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡ በተጨማሪ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ //ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡

8.ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡

9.በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡

10.ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ//ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡በተጨማሪ /ቤቱ የማይነበብ የሰነድ ኮፒ የመቀበል ግዴታ የለበትም፡፡

11.ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡

12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5(አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ//ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡

13. //ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96/ 046-212-65-95

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

Save Tender