Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ሚዛን አማን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0471355629
  • Website
  • Deadline01 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-01-01 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የህትመት ውጤቶች ግዥ ጨረታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በደ/ምዕ////መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 2018 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ //ቤቶች አገልግሎት የሚውል የህትመት ውጤቶች ግዥ ጨረታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በሚጠይቀው ዘርፍ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸው
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤
  5. ከግብር ዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
  6. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የህትመት ውጤቶች ግዥ 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 አምስት መቶ ብር /500 ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
  9. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣው 15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 830 ታሽጎ በዚያው ቀን 900 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471355629

 

በደ/ምዕ////መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

 

Save Tender