የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በዓለም ህጻናት መርጃ ድርጅት /UNCEF በተመደበ ገንዘብ ለመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተፋጠነ ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መማሪያ እና ማስተማሪያ መጻህፍትን በግልጽ ጨረታ ማሳተም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EB/EMAS/015/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በዓለም ህጻናት መርጃ ድርጅት /UNCEF በተመደበ ገንዘብ ለመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተፋጠነ ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መማሪያ እና ማስተማሪያ መጻህፍትን በግልጽ ጨረታ ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊና በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተፋጠነ ትምህርት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መማሪያ እና ማስተማሪያ መጻህፍት ቴክኒካል የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ (Specifcation) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600.00 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር103 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች መጻህፍቱን ለማሳተም እና አጓጉዞ ለማስረከብ የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ሲሆን ይህም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሐሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ በትምህርት ግብዓት ጥናትና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ ማስገባት የሚቻለው እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ በዋለ በ16ኛው ቀን ሲሆን ካላንደር የሚዘጋው በዓል፣ ቅዳሜና እሑድ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205654 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
