የፍ/ሰላም መም/ትም/ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ማለትም ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 ኮምፒውተርና ተዛማጅ፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች፣ ሎት 5 የህንፃ ዕቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና ዕቃዎች፣ ሎት 7 የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ ሎት 8 ቁሳቁስና ተገጣጣሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የፍ/ሰላም መም/ትም/ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ማለትም ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 ኮምፒውተርና ተዛማጅ፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች፣ ሎት 5 የህንፃ ዕቃዎች፣ ሎት 6 የመኪና ዕቃዎች፣ ሎት 7 የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ ሎት 8 ቁሳቁስና ተገጣጣሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃዱ በዘመኑ 2018 ዒ.ም የታደሰ መሆን አለበት፤ የግብርከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ነምበር ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ሰነዱ መሸጫ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ሲሆን በኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝርና መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ፣ ለሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000.00 /አስር ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገ/ያዥ ላይ ደረሰኝ በመቁረጥ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፖስታው ላይ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፍ/ሰላም መም/ትም ኮሌጅ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍ/ሰላም መም/ትም ኮሌጅ ገ/ፋ/ን አስ/ቡድን ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፣
- ተጫራቾች ሞልተው በሚያቀርቡት ሰነድ የባለቤትነት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን ፊርማና ማህተም ያለበት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ተወዳድረው የሚያሸንፏቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ሙሉ ወጪ ፍ/ሰላም መም/ትም ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ገቢ ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም መስሪያ ቤቱ 20% የመቀነስ የመጨመር መብት አለው።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ ውል ማስከበሪያ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ማሲያዝ ይኖርበታል፡፡
- በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ።
- አሸናፊ የሚመረጠው ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ በተያያዘው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መግለጫና በሚቀርበው ዝቅተኛ ዋጋ ሆኖ መስሪያ ቤቱን በሚጠቅም መሰረት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት ወይም በ 058 775 02 54 058 775 1270 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
የፍ/ሰላም መም/ትም/ኮሌጅ
