Tender Detail

Tender Details


በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ የእስቴሽነሪዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የተያዩ የተክል ዘር፣ የህንጻ ጥገና፣ የጉልበት ስራ፣ የአይቲ ዕቃዎች፣ መለዋወጫ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና ለአንድ አመት ኮንትራት የሚቆይ የዲኮርና ሳውንድ ሲስተም ኪራይ አገልግሎት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 005/00001/2018

 

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር 2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ዙር ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ የእስቴሽነሪዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የተያዩ የተክል ዘር፣ የህንጻ ጥገና፣ የጉልበት ስራ፣ የአይቲ ዕቃዎች፣ መለዋወጫ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገናና ለአንድ አመት ኮንትራት የሚቆይ የዲኮርና ሳውንድ ሲስተም ኪራይ አገልግሎት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ በገ//ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር (supplier List) ውስጥ የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀትና ማንኛውም ተወዳዳሪ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸው መረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በጨረታ መዝጊያ ሰዓት የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃ ዓይነቶች በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሊሆን ይገባል፡፡
  6. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውና አድራሻቸውን እንዲሁም ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም በማህተም ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ የሚወዳደሩትን የዕቃ ዓይነቶች ለይተው መፃፍ አለባቸው።
  8. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ዕቃዎችን ከወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት ጋር ውል በገባ 10 ቀናት ውስጥ ዕቃ ግምጃቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት አገልግሎት ወይም ወጪ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ... የተጫረቱትን ዕቃ ዋጋ ጠቅላላ ድምር በሎት 1.5% በካሽ ማሳያ ማዘዣ በኦርጂናል የጨረታ ሰነድ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. በጨረታው ያሸነፈው አካል ማሸነፉን እንደተገለጸለት ከመ/ቤቱ ጋር 10 (አስር) ቀን ቀርቦ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. በጨረታው ያሸነፈ አቅራቢ ውል ከጽ/ቤቱ ጋር ውል ማስከበሪያ ያስያዘው .... ተመላሽ አይሆንም፡፡
  12. በጨረታው ያሸነፈ አቅራቢ ውል ሲፈጽም የግዥውን አጠቃላይ ዋጋ 1.5 % ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  13. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. የጨረታ ሳጥን 10 ኛው ቀን ከቀኑ 1030 ታሽጎ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ይከፈታል 11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  15. በጨረታው ላይ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ 60 (ስልሳ ) ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0967670005/0911460014/09131479 51 በመደወል ከድሪም ላይነር ሆቴል ወረድ ብሎ ወይም ከናዝራ ሆቴል ፊት ለፊት የድሮ 35 ቀበሌ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በቂርቆስ /ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት

 

Save Tender