በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚሆን ቋሚ እቃዎች ማለትም ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በጨረታው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/0009/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚሆን ቋሚ እቃዎች ማለትም ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በጨረታው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለግዥ የቀረቡ እቃዎችና የጨረታ ማስከበሪያ CPO
- ሎት አንድ ለኤሌክትሮኒክስ፣ የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 ብር
- ሎት ሁለት:- ለፈርኒቸር፣ የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 ብር ስለሆንም ተወዳዳሪዎች:-
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫትና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በአላይን /online ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት።
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት የጨረታ ሰነዱ ጠቅሰው፤ በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ሕጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 ብር /አንድ መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከዝጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታው ሰነድ መግዛት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፣ ህ/ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በስም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21/ሀያ አንድ/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሠራት አለበት።
- የጨረታው ሰነድ በ21ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- በግዢ ኤጀንሲ በዕቃ አቅርቦት ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም
- የቫት 7.5 ለወረዳው ገቢ የሚቆርጥ
- ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፏቸው እቃዎች የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ መሆኑን፡
- ተጫራቾች ተጫርተው ያሸንፏቸው ማንኛውም እቃ የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማእከል ርቀቱ ከአዲስ አበባ 16ኪሜ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
ስልክ:- 0113360631/0113360146
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
መ/አምባ
