ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጸውን ያገለገለ ኪያሪዩ አዉቶሞቢል ጋምቤላ ከተማ ላይ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገለ ተሽከርካሪ ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ - 05/18
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለጸውን ያገለገለ ኪያሪዩ አዉቶሞቢል ጋምቤላ ከተማ ላይ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ለጨረታ የቀረበዉ ያገለገለ ተሸከርካሪ |
የተመረተበት ዓ/ም |
ብዛት |
|
1 |
ኪያሪዩ አዉቶሞቢል |
2005 |
01 |
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ያገለገለ ኪያሪዩ አዉቶሞቢል ጋምቤላ ከተማ ኬር የገበያ ማእከል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፣ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፤ ጋምቤላ ከተማ ኬር የገበያ ማእከል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ እና በተጨማሪም የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ፣ ቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በመገኘት ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀዉ መሰረት ስለዉቶሞቢሉ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አዉቶሞቢሉን ሲገዙ የሚችሱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ጋር አያይዘዉ በታሸገ ኢንቬሎፕ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ጋምቤላ ከተማ ኬር የገበያ ማእከል ፊት ለፊት በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታዉ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ/ም. ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጋምቤላ ከተማ ኬር የገበያ ማእከል ፊት ስፊት በሚገኘዉ ብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል አዉቶሞቢሉን ማንሳት ይኖርባቸዋል።
- ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
- የጨረታው አሸናፊዉ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል።
- ጨረታዉ ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለው።
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0910-663386 / 0475510379 / 0475510361 / 0116631729 /ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
