የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ
የሱቅ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር-RE-EMC/OT/THBD/RENT/02/2018
የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
ሱቁ የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታው መክፈቻ |
ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
|
1 |
የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን ሱቆች |
25 |
አዲስ አበባ |
22/04/2018 ዓ.ም |
4፡00 ጠዋት |
22/04/2018 |
4፡30 ጠዋት |
አ.አ ዋናው መሥሪያ ቤት |
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች (መመሪያዎች) ፡-
- የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ብሎክ 2፤ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት በግንባር በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በሶፍት ኮፒ በሲዲ (soft copy) መግዛት ይችላሉ፤
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለኪራይ የተዘጋጁትን ሰቆች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 1፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ለመክፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ሱቆች በሚገኙበት ቦታዎች በአካል በመገኘት ኮርፖሬሽኑ በሚመድበው ሰራተኛ አስጎብኚነት መመልከት ይችላል፡፡ የሱቆቹ ብዛት እንደአስፈላጊቱ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች የሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ከሰነዳቸው ጋር የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ለሆኑትና ያስያዙት ሲፒአ (CPO) ህጋዊ ባንክ ከሆነ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ሊታሰብላቸው ይችላል ወይም ለተሸነፉት ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ለሱቅ ኪራይ ቅድሚያ የሶስት ወራት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በላዩ ላይ ድርጅቶች ከሆኑ ማህተም ያረፈበት፣ የግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ሶስት ፊርማ በመፈም ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መዝጊያ እና መከፈቻ ቀንን በተመለከተ ከላይ በሰንጠረዥ ዋናው መ/ቤት በተገለጸው ቀን እና ሰዓት መሰረት ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች ስፋት ካሬ ሜትር ዋጋ በቁጥርና በፊደል ስርዝ ድልዝ የሌለበት በግልጽ ሞልተው በታሸገው ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን ግዥ የሚሆነው የነጠላ ዋጋው ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0911622263 ወይም 0911008854 /ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተከራዮች ሱቆችን ለጌጣጌጥ፣ ለማእድን ውጤቶች፣ ለባህላዊ አላባሳት እና ቅርጻቅርጾች መሸጫ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎት የሚከራዩ ይሆናል፡፡ ከአልኮሆል መጠጥ ውጭ።
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
+251-0911622263 ወይም 0911008854
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን አዲስ አበባ
