Tender Detail

Tender Details

  • Company የምዕ/ሸ/ዞን ማረሚያ ቤት
  • Address የምዕ/ሸዋ ዞን : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-236-20-82
  • Website
  • Deadline29 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Firewood , Merchandise

የምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከጥር 01/2018 እስከ ጥር 30/2019 ድረስ ለ (አንድ) አመት የሚቆይ በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አይነት ጥሬ የእህል ምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት፣ የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት ለህግ ታራሚዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1

 

የምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከጥር 01/2018 እስከ ጥር 30/2019 ድረስ (አንድ) አመት የሚቆይ በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አይነት ጥሬ የእህል ምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት ለህግ ታራሚዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማህበራትም ሆኑ ግለሰብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያ ማሟላት አለባቸው

  1. በንግድ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡ የግብር ከፋይነት (TIN NO) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የቫት ከፋይነት እንዲሁም የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይውሎ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 430 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የህግ ታራሚዎች ኮሚቴ የማረሚያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ እና ከዞኑ አቃቢ ህግ ቢሮ እንዲሁም ከዞኑ //ትብብር በሚወከሉ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስሪያቤቱ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  5. የበሰለ ምግብ አቅርቦት በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ከተከፈተ ለጨረታው ያቀረቡት ሀሳብ መቀየር ወይም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው ራስን ማግለል አይችልም፡፡
  7. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት አንስቶ 3 ቀን ውስጥ ማረሚያ ቤት በመቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ /ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማረሚያ ቤት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውና የውል ማስከበሪያ በጥቃቅንና አነስተኛ ደንብ 192/2009 ተሻሽሎ በወጣው አንቀፅ 27 መሰረት ከአደራጁ ክፍል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው
  10. ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት C.P.O ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ምግቡ የሚዘጋጀው በመስሪያ ቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሆኖ በማብሰያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች የማረሚያ ቤቱ እንዳለ ሆኖ የጎደለውን ጨረታውን ያሸነፈው ማህበራት ወይም ግለሰብ የማሟላት ግዴታ አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ለማ/ቤቱ ለበላይ አካሎች ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 5 ቀን ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ ይችላል፡፡
  14. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- ምዕ//ዞን///ልማት/ትብብር /ቤት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-236-20-82 /011341-00-23

 

የምዕ//ዞን ማረሚያ ቤት

 

Save Tender