Tender Detail

Tender Details


የልደታ ከፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽህፈት ቤትና አስተዳደርና ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ልዩ ልዩ የህትመት ሥራዎች፣ የተለያዩ ሽልማት እቃዎች እና የጉልበት ስራዎች ዕቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 የጨረታ ቁጥር 02/2018

 

የግልፅ ጨረታ ዙር 02/18 በልደታ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀ/ል/ ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥና አስተዳደር ቡድን ግዥ ግልፅ ጨረታ

  1. ሎት 1. ልዩ ልዩ የህትመት ሥራዎች የአገልግሎት ግዥ
  2. ሎት 2. የተለያዩ ሽልማት እቃዎች
  3. ሎት 3. የጉልበት ስራዎች ዕቃዎች ግዥ

በዚህም መሰረት ፡- በጨረታ ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ማሟላት የሚገባቸው

  1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና በሚወዳደሩበት መስክ ከንግድ ፈቃዱ ጀርባ ገላጭ መሆን አለበት ፤ የግብር መክፈያ መለያ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፤ተጨማሪ 15 % እሴት ታክስ ሰብሳቢ ምዝገባ ፤በአቅራቢዎች ዝርዝር ቀጥታ ከዘርፉ ጋር የተጣጣመ ምዝገባ ኮፒ ሰርተፍኬቶች እንዲሁም ወቅታዊ የሆነ ክሪላንስ እንዲሁም ለጉልበት ሥራ ተጫራቾች ከተደራጃችሁብት ወቅታዊ የሆነ ደብዳቤ ማስረጃዎች ግልፅና ተነባቢ መሆን አለበት በእነዚህ ኮፒ ማስረጃዎች የድርጅትዎ ማህተም ከጀርባው ይደረግበት፡፡

ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፍል ልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል ፡፡ እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ የምትጫረቱ ተጫራቾች ሰነዱን የምታገኙት የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ህንፃ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ነው፡፡

ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በመስሪያ ቤታችን ስም በልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥና አስተዳደር ቡድን ስም ሲፒኦ አሰርተው ቴክኒካል ኦርጅናል ተብሎ በተሰየመው ፖስታ ማስገባት አለባቸው ፡፡ ሲፒኦ ሲያሰሩ በሚወዳደሩበት በድርጅት ስም እንዲያስገቡ

ሎት 1 ፡- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 ሎት 2፡- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ሎት 3 ፡- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 እየገለፅን ሎቶችን ጠቅልሎ ሲፒኦ ማሰራት ከውድድር ውጪ ስለሚያስደርግዎ ሲያሰሩ በእያንዳንዱ ሎት በመለየት ለየብቻ ሲፒኦ ያሰሩ፡፡

በተጨማሪ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ከሚመለከተው ተቋም ኦርጅናል ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ ከሰነዳቹ ጋር ማያያዝ አለበት፡፡

ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ኢንቮሎፕ ሲያስገቡ የሚወዳደሩበትን የሎት ቁጥር መጥቀስና ፋይናንስ ከሆነ ፋይናንስ ኦርጅናልና ኮፒ 1 ቴከኒክ ከሆነ ቴክኒክ ኤርጅናልና ኮፒ ፣ በማለት በሁለት ኤንቩሎኘ የሚከቱበት ፖስታ ላይ የሎት ቁጥሩንና ኦርጅናልና ኮፒ በመፃፍ እንዲያስገቡ እያሳሰብን ሲፒኦ ቴክኒካል ኦርጅናል ብለው በለዩት ፖስታ ውስጥ ይክተቱ ፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደራችሁበት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ነገር ግን ቴክኒክ በሚለው ፖስታ ውስጥ የዋጋ ዝርዝር ሳይጨመርበት ሌሎች ተፈላጊ ማስረጃ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡እንዲሁም በመስክ ጉብኝት ጊዜ ለሚመለከታቸው ተባባሪ በመሆን ገለፃ ማድረግ ይጠበቃል ፡፡
  2. የጨረታው ሰነድ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ቀኑ 11፡00 እንዲያስገቡ እያስታወስን በዕለቱ በ11፡00 የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን የመክፈቻው ቀን በ11ኛው ቀን ሲሆን ነገር ግን ቅዳሚና እሁድ ወይም በብሔራዊ በዓል አማካኝነት ዝግ ከሆነ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት 6ኛ ፎቅ አሰተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 605 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የተጫራች ወይም ወኪል አለመኖር ጨረታው ከመከፈት አያግደውም ፡፡
  3. ከመስሪያ ቤታችን የገዙት የጨረታ ሰነድ ውስጥ ክፍል 4 ላይ በተዘረዘሩት ላይ ዋጋ እንዲሞሉ እያሳሰብን ነገር ግን ከመ/ቤታችን ቅፅ ውጪ የሞሉት ሰነድ ከውድድር ውጪ ይደረጋል ፡፡ እንዲሁም በሰነዱ ውስጥ ምንም አይነት ሌላ ፅሁፍ መፃፍ የለባቸው፡፡
  4. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ፅሁፍ በእርሳስ የተፃፈ እና በሞሉት ዋጋ ላይ ስርዝ ደረልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ለግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ያቀርባል ።
  6. መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. አሸናፊ ወይም የተመረጠ ተጫራች ተፈፃሚ የሚሆነው በውላቸው ስምምነት መሠረት ነው፡፡

ማስታወሻ፡- በጨረታው ተካፋይ ከሆኑ ተፈላጊ ሰነዶች ፖስታ ውስጥ ከመክተትዎ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመጀመርያው ገፅ ላይ የሚገኘውን ማስታወሻ በትኩረት ይመልከቱ: ወይም ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥና አስተዳደር ቡድን 6ኛ ፎቅ በአካል ቀርበው መረጃ ማግኘት ይችላሉ በተጨማሪ በስልክ ቁጥር 0118-55-25-49 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

አድራሻችን ፡- የልደታ ከፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤትና አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ነው ልደታ ኮንዶሚኒየም በላይ ተክሉ አጠገብ የሚገኘው ነው።

 

የልደታ ከፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤትና አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender