በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለቂልጦ ጎሞሮ ማዘጋጃ ቤት እና ለቡጫ ማዘጋጃ ቤት ለጠጠር መንገድ ግንባታ የሚሆን ጠጠር ለማምረት እና አዲስ መንገድ ለመክፈት ዶዘር በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለቂልጦ ጎሞሮ ማዘጋጃ ቤት እና ለቡጫ ማዘጋጃ ቤት ለጠጠር መንገድ ግንባታ የሚሆን ጠጠር ለማምረት እና አዲስ መንገድ ለመክፈት ዶዘር በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ፡-
ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጠጠር መንገድ ግንባታ የሚሆን ጠጠር ለማምረት እና አዲስ መንገድ ለመከፈት ዶዘር ማሽን ኪራይ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200(ሁለት መቶ) ብር በመከፈል በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት
በዚህ ጨረታ ስመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በአከራይነት ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ።
2. የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያው /CPO/ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት የማስጫኛና የማውረጃ ጨምሮ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
6. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
7. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ወረዳው ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን
የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
