ሲዳማ ኤልቶ ኃ/የተወሰነ ኅብረት ስራ ዩኒየን ከ01/02/17 እስከ 30/01/18 ዓም ድረስ ያለውን ሂሳብ የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ኤልቶ ኃ/የተወሰነ ኅብረት ስራ ዩኒየን ከ01/02/17 እስከ 30/01/18 ዓም ድረስ ያለውን ሂሳብ የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም እሱ በሚወከለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፈቃድ ያገኘ እና የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ፈቃዱን ያሳደሰ
- የሂሳብ ሙያ ፈቃድ ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- በህብረት ስራ ማህበራት ኦዲት ልምድ ያለው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውንና ዶክመንታቸውን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒው ለየብቻ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ህጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ7ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሚያስገቡ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ በ11፡30 የሚታሸግ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት/ባልተገኙበት በ8ተኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- ፅ/ቤት ድረስ በአካል በመቅረብ አልያም በስ.ቁ
0930108356/0979886416
046-212-4704 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅ/ስራ ዩኒየን ኃ/የተ
