በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውል ETOL በጀት ከዚህ በታች በሎት በቀረበው ዝርዝር መሰረት ግዥ ለመከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 07/2018
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውል ETOL በጀት ከዚህ በታች በሎት በቀረበው ዝርዝር መሰረት ግዥ ለመከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም፡-
- ሎት 1. ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች የአካል ድጋፍ ቁሳቁስና የትምህርት መረጃ መሳሪዎች ግዥ፣
- ሎት 2. ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች የሞንቶሶሪ የትምህርት መረጃ መሳሪዎች ኪት ግዥ፣
- ሎት 3. የሞንቶሶሪ ሸልፍ የቢሮ ፈርኒቸር ግዥ፣
- ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ ግዥ፣
- ሎት 5. የመሬት ምንጣፍ ግዥ፣
ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና ያላቸው መሆን አለባቸው፤ የተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፤
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 – 6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 21ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በሲፒኦ ወይም አንኮንድሻናል ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በ2 ፖስታ በማሽግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በማሽግ ማቅረብ አለባቸው፤
- ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ቁጥር 14 ማግኘት ይቻላል። አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም።
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር፡- 046212-43-02/03
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
ሀዋሳ
