የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በኩል የደን ዘር ግዥ፣ በካልም ፕሮግራም በጀት መሬት ልከት የሚያገለግሉ ቀለም እና የጽ/መሳሪያዎችና አላቂ ዕቃዎች፣ የህትመት ግዥ፣ የግብርና ቴክኖሎጂ ግብዓቶች ግዥ እና የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ግዥዎችን በሎት በማለየት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ የጨረታ ቁጥር 01
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በኩል የደን ዘር ግዥ፣ በካልም ፕሮግራም በጀት መሬት ልከት የሚያገለግሉ ቀለም እና የጽ/መሳሪያዎችና አላቂ ዕቃዎች፣ የህትመት ግዥ፣ የግብርና ቴክኖሎጂ ግብዓቶች ግዥ እና የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ግዥዎችን በሎት በማለየት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- የደን ዘር ግዥ
- ሎት 2፡- የመሬት ልከት የሚያገለግሉ ቀለም ፣ የጽ/መሳሪያ እና የአላቂ ዕቃዎች
- ሎት 3፡- የህትመት ግዥ
- ሎት 4፡- የግብርና ቴክኖሎጂ ግብዓቶች የጥድ ጣውላና የህንፃ መሳሪያ ግዥ
- ሎት 5፡- የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶችን የማሟላት ግዴታ አለባቸው፡፡
1ኛ. በዘርፉ የታደሰ የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ህጋዊ ፍቃድ ሰርቲፍኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
2ኛ. የንግድ ስራ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
3ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
4ኛ. የቲን ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ወርቀት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5ኛ. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ ስም በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000454620918 ገቢ በማድረግ አድቫይስ በመያዝ ከግዥ/ክ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት መውሰድ ይቻላል፡፡
6ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሎት1፣ የሎት2፣ እና የሎት3 ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ ሲሆን የሎት 4፣ 60,000.00 /ስልሳ ሺህ/ እና የሎት 5፣ ደግሞ 30,000.00 /ሠላሳ ሺህ ብር/ ማቅረብ የሚገባቸው በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም (cpo) ሲፒኦ ፣ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት (L/C) የቀረበ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና እንድ ኮፒ በተለያዬ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታ ለ15ኛ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ ግዥ /ከ/ንብ/አስ/ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
8ኛ. ጨረታው በአዲሰ ዘመን ጋዜጣ በወጣው 16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 የጨረታ ሳጥን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ በግ/ክ/ ንብ/አስ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡
9ኛ. የጨረታ መዝግያ ወይም መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት እና ቀን ይሆናል።
10ኛ. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
11ኛ. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ስ.ቁ. 0473312048 / 0473312145
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ
ቦንጋ
