ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በበጀት ዓመቱ እቅድ መሰረት በድርጅቱ ለታቀፉ ተማሪዎች የሚሆን የመማሪያ ደብተር እና እስክሪብቶ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን በበጀት ዓመቱ እቅድ መሰረት በድርጅቱ ለታቀፉ ተማሪዎች የሚሆን የመማሪያ ደብተር እና እስክሪብቶ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የዕቃው አይነት
|
መለኪያ
|
ብዛት
|
ምርመራ/ አስተያየት
|
|
1
|
ደብተር ባለ 50 ገጽ፣ ሲንግል ላይን፣ በፕላስቲክ የተለበደ እና 22*16 ሴ.ሜ |
በቁጥር
|
77376
|
|
|
2
|
እስክሪብቶ ኦርጅናል
|
በቁጥር
|
77376
|
|
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ቢያንስ የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የዘመኑ የታደሰ የንግድና የታደሰ የዋና ምዝገባ ፈቃዳቸውን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት፣ በጨረታ እንድትሳተፉ ለዘመኑ በጀት ዓመት ብቻ የሚያገለግል የምስክር ወረቀት እና ቲን ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30- 6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11:30 ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ ዲላ በሚገኘው ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ጽ/ቤት ሂሳብ ክፍል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒውን በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ(ፖስታ) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% ሲፒኦ በሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ስም ተሰርቶ በኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ውስጥ በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሰባተኛው/7ኛው/ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ድረስ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ደብተር እና እስክሪብቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-331-0049/ 046-331-3145 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅና መረዳት ይቻላል።
አድራሻ፡ ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ዲላ ከተማ ከዲላይት ኢንተርናሽናል ሆቴል 100 ሜትር ገባ ብሎ።
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ
